የሪያል ሶሴዳዱ ዋና አሰልጣኝ ኢማኖል አልጓሲል በዛሬው ጨዋታ የአሸናፊነት ግምቱን ለቡድናቸው የሚሰጡ ሰዎች “ኳስ የማያውቁ ናቸው” ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ በሊጉ ጥሩ ውጤት እያገኙ ባይሆንም “ምርጥ አሰልጣኝ ያለው ምርጥ ቡድን ነው” ሲሉ አሰልጣኙ ተናግረዋል።
አክለውም “የአሸናፊነት ግምቱን ለሪያል ሶሴዳድ የሚሰጡ ሰዎች ምንም የእግርኳስ እውቀት የሌላቸው እና ተጋጣሚያችንን የማያውቁ ናቸው” ብለዋል።
“ለእኔ ማንችስተር ዩናይትድ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን የማሸነፍ ግምት የምሰጠው ክለብ ነው” ሲሉ ኢማኖል አልጓሲል አስረድተዋል።