የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ከዛሬው የሪያል ሶሴዳድ ጨዋታ በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቡድናቸው በውጤት ማጣት ውስጥ ቢገኝም ሩበን አሞሪም “ምንም ቢፈጠር አጨዋወቴን አልቀይርም” ሲሉ ጽኑ አቋማቸውን አሳውቀዋል።
“አጨዋወታችን ችግር የለበትም” የሚሉት አሰልጣኙ “ሌሎች በርካታ ችግሮች አሉብን፣ እነሱን ለመፍታት ጥረት እያደረግን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
አክለውም በአጨዋወት ዘይቤያቸው የወደፊት ስኬታማነት “አልጠራጠርም” ሲሉ፣ ይህንን አቀራረብ ምንም ቢፈጠር በፍጹም ስለመቀየር እንደማያስቡ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ከምሽቱ 2:45 ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ከሜዳው ውጪ የዩሮፓ ሊግ ጨዋታውን ያደርጋል።