ናይጄሪያዊው የፊት መስመር አጥቂ ኦድዮን ኢግሀሎ ማንችስተር ዩናይትድ ሊያስፈርመው እንደሚፈልግ ሲሰማ ፀሎት ጀምሮ እንደነበር ገልጿል።
“ዩናይትድ ለሁለተኛ አጥቂነት እንደሚፈልገኝ ወኪሌ ሲነግረኝ አራት አማራጭ ነበራቸው እኔ ሶስተኛ ነበርኩ የሌሎች እንዳይሳካ ወዲያው ነው ፀሎት የጀመርኩት” ሲል ኢግሀሎ ተናግሯል።
አክሎም “ወኪሌ ገንዘብ ባይከፍሉኝም እንኳን ዝውውሩ እውን እንዲሆን እንዲያደርግ ጠይቄዋለሁ ማልያውን መልበስ ፈልጌ ነበር” ብሏል።
በአሁኑ ሰዓት በሳውዲ አረቢያ ሊግ የሚገኘው ኦድዮን ኢግሀሎ በማንችስተር ዩናይትድ በነበረበት ሰዓት ሀያ ሶስት ጨዋታዎች አድርጎ አምስት ግቦችን አስቆጥሯል።