ጀርመናዊው አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሊቨርፑል ፕርሚየር ሊጉን ካሸነፈ በድል ዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
“ከሊቨርፑል ጋር የሊግ ዋንጫውን ድል ለማክበር አቅጃለሁ” ያሉት የርገን ክሎፕ ነገርግን በባሱ ውስጥ አይደለም ብለዋል።
እስከአሁን ወደ አንፊልድ ለምን እንዳልሄዱ ያብራሩት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ለቡድኑ መጥፎ እድል እንዳልሆን በመፍራት ነው ብለዋል።
“ሊቨርፑል ያለማቋረጥ እያሸነፈ ነው ወደዛ ከሄድኩ ይሸነፋሉ ብዬ እፈራለሁ ስለዚህ ሊጉን ማሸነፉን ካረጋገጠ በኋላ መሄድ እመርጣለሁ” ሲሉ የርገን ክሎፕ ተናግረዋል።