Wednesday, March 12, 2025
HomeSportሜሲ በምሽቱ ጨዋታ ለምን አልተሳተፈም?

ሜሲ በምሽቱ ጨዋታ ለምን አልተሳተፈም?

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ኢንተር ሚያሚ ዛሬ ሌሊት ባደረገው የሻምፒዮንስ ካፕ ጨዋታ ሳይሳተፍ ቀርቷል።

ሊዮኔል ሜሲ በጨዋታው ያልተሳተፈው በመጠነኛ ጉዳት ምክንያት ሀኪሞች በሰጡት ትዕዛዝ መሆኑን የቡድኑ አሰልጣኝ ማሼራኖ ተናግረዋል።

ኢንተር ሚያሚ ሊዮኔል ሜሲን በጉዳት ለረጅም ጊዜ ላለማጣት ባለፉት ጨዋታዎች ቅድመ ጥንቃቄ እያደረገ መሆኑ ተዘግቧል።

ሊዮኔል ሜሲ በኢንተር ሚያሚ ማድረግ ከነበረበት ሰባ አንድ ጨዋታዎች በአርባ ሁለት ያህሉ (59%) መሳተፉ ተነግሯል።

ኢንተር ሚያሚ ከካቫሌር ጋር ያደረገውን የ “CONCACAF” ሻምፒዮንስ ካፕ ጨዋታ በአሌንዳ እና ሱዋሬዝ ግቦች 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

RELATED ARTICLES
- Advertisment -

Most Popular

Recent Comments